የናይል ተፋሰስ ሃገሮች ግብፅ እንድትመለስ ጠየቁ

ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ውስጥ የተሰበሰቡት የናይል ወንዝ የትብብር ጅማሮ ወይም ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የውኃ ሚኒስትሮች ግብፅ ወደ ትብብር መድረኩ አባልነት እንድትመለስ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ ሱዳን አቋርጣው ወደነበረው የኢኒሼቲቩ አባልነቷ ሙሉ የመዋጮ ውዝፍ ዕዳዋን ከፍላ መመለሷን ዋና ፅሕፈት ቤቱ ካምፓላ-ዩጋንዳ የሚገኘው የናይል ትብብር አካባቢያዊ ድርጅቱ /ኤንቢአይ/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ በየነ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሰባት የናይል ቤዚን ወይም የናይል ተፋሰስ ሃገሮች የተፈረመውንና እስከአሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሃገሮች በየፓርላማዎቻቸው ያፀደቁትን የናይል ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ዩጋንዳም ልታፀድቀው መሆኑን የሃገሪቱ የውኃና የአካባቢ ሚኒስትር መናገራቸውን መገናኛ …