ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አውራምባ ታይምስ
ግርማ ካሳ
ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር አንድ ወቅት፣ የቅንጅት አመራር አባል የነበሩ ጊዜ በጣም ወዳጆች ነበርን። ላለፉት አምስት አመታት ግን ተራራቅን። አለመስማማት በመካከላችን ተፈጠረ። እርሳቸው አንድ መንገድ ያዙ። የጦርነት መንገድ! ከማይመቹን ቡድኖች ጋር ማበር ጀመሩ። በተለያዩ ጊዜያት የሚመሩት ድርጅት የሚያራምዳቸውን ፖሊሲዎችን መንቀፍ ጀመርን። የፖለቲካ ልዩነት ባህል ብዙ ያልገባቸው የርሳቸው ደጋፊዎች ተነሱብን። “ግንቦት ሰባትን ለምን ትናገራላችሁ?” በሚል ወያኔ ተባልን።