በሰሜናዊ በኬንያ በተደጋጋሚ የሚደርሰዉ ጥቃት

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በኬንያ በተከሰተ የጎሳ ግጭት ቢያንስ 16 ተገደሉ ወደ 20 የሚሆኑ ሰዎች ደሞ ቆሰሉ። በሰሜናዊ ኬንያ ማንዴራ በተሰኘዉ መንደር በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያ የተቀሰቀሰዉ ይህ የጎሳ ግጭት፤ በሶማልያ ጎሳዎች መካከል እንደሆነም ታዉቋል።