በኢትዮጵያ የርቀት ትምህርት ታገደ

የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር ከ2003 ዓም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጥ የነበረው የርቀት ትምሕርት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ያወጣው መመሪያ እያነጋገረ ነው።

የትምሕርት ሚኒስቴር መመሪያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ የመጣውን የትምሕርት ጥራት ደረጃ ለማሻሻልና ከሐገሪቱ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ዓለም ዓቀፍ ደረጃን የጠበቀ ሰልጠና ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጿል ። በአንፃሩ እገዳው ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መጣሉን የሚቃወሙት የግል ዩኒቨርስቲዎች ና ኮሌጆች የትምሕርት ደረጃን ለማስጠበቅ ዓለም ዓቀፍ መስፈርትን አውጥቶ መስራት እንጂ መመሪያ ጥራት ማስጠበቅ አይችልም ሲሉ ይከራከራሉ ።

ያዳምጡ