የተንዳሆ ፕሮጀክት የጉልበት ሠራተኞች ፍላጐትና አቅርቦት አለመጣጣሙ ተገለጸ

– በአምስት ወራት ውስጥ 3,969 ሠራተኞች መፍለሳቸው ይነገራል

መንግሥት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት የጀመረው የተንዳሆ የሸንኮራ አገዳ ፕሮጀክት የጉልበት ሠራተኛ ፍላጐትና አቅርቦት ሊጣጣም አለመቻሉን አንድ የፕሮጀክቱ ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡