እጀ ብልህ መሪና ደጋፊዎቹ
ታክሎ ተሾመ
አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በድርጅት፤ በቡድን፤ በተናጥል የሚደረጉ የመፈክር እንቅስቃሴ መኖራቸው ያለና የሚጠበቅ ነው። በሁሉም ዘንድ የሚደረጉ መፈክሮች የሩቅና የቅርብ ዓላማን የሚያመላክት መሪ ቃል ቢሆንም ፍሬ ቃሉ በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የመፈክሮችን ይዘት ድርጅቶችም ሆነ ደጋፊዎች የሩቁንም ሆነ የቅርቡን ዓላማ ሳያሳኩ መንገድ ላይ ወደ ኋላ መመለስ የሚታይበት አጋጣሚ ብዙ ነው።