ሥር ነቀል ወይሰ ሰር በቀል ለውጥ ? ከሎሚ ተራ ተራ…….

“ለመብቀል ለመብቀል፤ ሰንዴውም ይበቅላል።
ለመብቀል ለመብቀል ቦቆሎም ይበቅላል።
ለመብቀል ለመብቀል አረሙም ይበቅላል።
ቦቆሎው ከአረሙ ሰንዴም፤ ከእንክረዳዱ በተግባር ይለያል።”

ክቡራን አንባቢያን ሆይ ለመሆኑ ወያኔ አገር በቀል፤ አጥፊና ላለፉት 22 ዓመታት ሕዝብን የገደለ፤ ያፈነ ያሰደደ፤ ያሰረና ያፈናቀለ፤ አሁንም ድረሰ በመግደልና በማፈን እንዲሁም በዝርፊያላይ የተስማራ ክፉ፤አገር በቀል ሰረአት ለመሆኑ ምሥክር መቁጠር ያሰፈልጋል ትላላችሁ?
“ወችው ጉድ፤ አሉ ብላታ;፤…………..፤ መቼም ጆሮ አልሰማ አይልምና: በተቃዋሚው ጎራ ዘወትር አሰደንጋጭና አሰገራሚ ውይይቶችን መሰማት የቀን ከቀን ክሰተት ቢሆንም ቅሉ፤ እኔን በእጅጉ ያሰገረመኝ ግን የወያኔን ሰርአት በሰመ “ሪፎርሜሸን (reformation) “ጠግነን ጠጋግነን መልሰን እናሰቀምጥ የሚለው ተቃዋሚነኝ ተብዬው ጎራ ነው። መጠርጠር አሁን ነው አለ ,፣ያገሬሰው”
“ ጠርጥር፣ ጠርጥር ፤ ገንፎ ለሥልሦ ቢገባም
አያጣም ሥንጥር” አትሉኝም፤-“

ከዛ በፊት ግን ሪፎርሜሽን (Reformation) (ማሻሻያ) ማለት ምን ማለት ነው?። መልሱን እናንተው መልሱ። እኔ ግን ይህቺን አንድ ምሳሌ ጣል ላድርግና ወደሌላኛው ልለፍ።

አሁን በአዐምሮችሁ አንድ ቆንጆ ቤት ሳሉ፤ ይኸ ቤት መሰረቱ በባለሞያ መሀንዲሰ በደንብ የተገነባ ነው። ይኸ ማለት ቤቱ በምን ያህል ካሬሜትር ቦታ ላይ እንደሚሰራ፤ ምን የህል ሲሚንቶ ምን ያህል አሸዋና ሌሎችም ሌሎችም፤ ብቻ አንድ ቤትን ጥሩ ቤት ነው ሊያሰኙ የሚችሉትን ያሟላ ነው።

ከጥቂት አመታት በኸላ ግን ባለቤቱ መሰኮቱ ጥሩ ጸሃይ አላሰገባ አለ በሩም በደንብ አልከፈት አለ፤ በሚል ሁኔታ ሁለቱንም መቀየር ፈለገና በዙ መድከም ሣያሰፈልገው ባለሞያ አናጢ አማክሮ አሮጌውን (ጸሃይ) አላሰገባ ያለውን መሰኮትና በደንብ አልከፈት ያለውን በረ አሰቀየረውና ጽሃዩም በደንብ ይገባ ጀመር በሩም ወለል ብሎ ይከፈት ጀመር እላችሁ አለሁ።

የፖሎቲካ ማህደሩ በሰነሰርአቱ ከተዘረጋ ከላይ እንደተመለከታችሁት ቤት አልመችና አልሰራ ያለውን ያለ ብዙ ችግርና ውጣ ውረድ ማሻሻልና መቀየር ይቻላል። ቸግሩ ግን

ግን ቀድሞውኑ ባልተመሰረተ ነገር ሰለማሻ ሻያ፤ (ሪፎረሜሸን) ( Reformation) ትንታኔ ለመሰጠት መንደርደሩ አይመሰላችሁም ?

ከዛ በፊት ግን አሁንም እሰቲ በቅድሚያ መኖር ሰለሚገባው ነገር እንጠይቅ ? ፖሎቲካል ኢኒሰቲቲዩሽን (political Institution) ማለት ምን ማለት ነው? ብለን እንጠይቅና መልሰ እናግኛ፤ አለ እንዴ ግን ? መች አጣችሁት፤

ፖሎቲካል ኢኒሰቲቲዩሸን ማለት፤-(political Institution) :- በህግ የበላይነት የሚያምን ፤ ሁሉን ያማከለ ህግን መተዳደሪያው ያደረገና መንግሰታዊ መሰተዳድሮችን፤ የመሀበራዊ መሰተዳድርን ለህብረተሰቡ በመፍጠር ምሳሌ በመሆን ሌሎች የፖሎቲካ ድርጅቶች ያለምንም ጫና እንዲመሰረቱ የሚያመቻች፤ የንግድ ተቋማት በአግባቡ እንዲመሰረቱና ያለችግር መንቀሳቀሰ እንዲችሉ የሚፈጥርና የሚያመቻች፤ ሁሉም እኩል የሚዳኝበት ፍርድቤት ያለውና የሰልጣን ሳይሆን የህግ የበላይነትን በማራመድ በዚሁ አላማ የመምረጥና የመመረጥን መብት ያከበረና የሚያሰከብር ተጠያቂነትም እንዳለ አምኖ የሚመሰረት የፖሎቲካ ድርጀት ማለት ነው።

ከላይ በዝርዝር ለመመልከት የሞከርናቸው ግን እንኳን መመሰረትና በሀሳብ ደረጃም እንደሌሉ ግን አፋኙ ወያኔ (TPLF) ላለፉት 22 አመታት ለሕዝብም ሆነ ላለማቅፉ ሕብረተሰብ አረጋግጠውልናል። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው የእደሳ ወይም ማሻሻያ (Reformation) የሚታሰበው? የሌለና ያልተመሰረተ ነገርሰ እንዴት ይታደሳል? መልሱን እናንተው መልሱ።

ለመሆኑ በአንድ አገር የሰረአት ማሻሻያ ለውጥ ለማምጣት አሰፈላጊ ናቸው፤ ለውጦቹንም ውጤታማ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፤ ከሚበሉት ዋና ዋናዎቹ ምንድናቸው ትላላችሁ? የኔን በከፊል እንደሚከተለው ጠቆም ጠቆም ላድርግና የናንተን ደግሞ እናንተ ጨምሩበት፡፡
ሪፎርሜሽን ሲታሰብ ፤ለተግባራዊነቱ፤ በቅድሚያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በሃገሩውሰጥ መኖራቸውን ማረጋገጥ በጣም አሰፈላጊ ነው።

1ኛ) በሃገሩ ውሰጥ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት መኖሩንና የዲሞክራሲ ሰርአት ቢያንስ ቢያንሰ ጭላንጭሉ እንኳን ያልጠፋ ለመሆኑ ማረጋገጥ ሲቻል።
2ኛ) መንግሰት ነኝ ተብዩው የህግ የበላይነትን የተረዳና አክባሪነቱም ባለማቀፉ ታዛቢዎች ዘንድ የተረጋገጠ መሆን ሲቻል።
3ኛ) በማንም እና በምንም አይነት ሁኔታ ጫና የማይደረግበት ለሕዝብ ግልጥ የሆነ ሚዲያ መኖሩን ማረጋገጥ ሲቻል።
4ኛ) ከፖሎቲካ ነጻ የሆኑ መሃበራት (Institution) ለምሳሌ የትምህርት፤ የመምህራን ማህበር፤ ባንክ ፤እነዲሁም ሌሎች መሃበራዊ ተቆማት ያለምንም ተጽዕኖ መንቀሳቀሰ መቻላቸውን ማረጋገጥ።
5ኛ ከሁሉም በላይ የሰበአዊ መብት እረገጣ አለመኖሩ ባለማቀፉ የሰባዊ መብት ተቆርቆሪ ድርጅቶች ማረጋገጥ ሲቻል።

እነግዲህ ባለማቀፍ መሰፈርት ከላይ የተዘረዘሩት አንዱም እንኳን በማይታዩበት እንዴት አይነት ጥገና ለማደረግ እነደሚታሰብ አላውቅምና፤ ሰንወያይ ይህንን ሁሉ ግምት ውሰጥ እያሰገባን ቢሆን መልካም ነው እላለሁ።
ሥለዚህ የሚያሰፈልገን ያለጥርጥር ሥርነቀል ለውጥ ነው። የተነቃነቀም ጥርሰ ሣይነቀል አይድንም፤ ነውና ተባብረን እንንቀለው እያልኩ መጣጥፌን ለጊዜው እዚህ ላይ ላብቃና፣ ውሃ ፉት ልበል።

በቸር ይግጠመን፤ አሰተያየትዎን/ ነቀፌታዎንም

ሎሚ ተራ ተራ ፡= [email protected] Friday, May-24-13