የሙስናው እስር ምስጢር!
ማረ በላዎቹ ርስ-በርስ ተበላሉ!
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
ለብዙዎች “ሙስና” የሚለው ቃል በ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረ ሃይለ-ቃል ይመስላቸዋል። ነገር ግን አይደለም። ቃሉ ግዕዝ ነው። ትርጉሙም፣ “ጥፋት” ማለት ነው። በአማረኛም የኖረ ሕዝባዊ ግጥም/አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው።
“የከንሯ ለዛ፣ የጉንጯ ሙስና፤
“ዐርብ ሮብ ያስክዳል፣ እንኳን ዐሙስንና።” ይላል – አዝማሪም።