ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል
ፍቅር ለይኩን
በቅርቡ ሙስጠፋ አል ላባድ የተባለ ሊባኖሳዊ ፖለቲከኛና ጸሐፊ Egypt is Battling Ethiopia over the Nile Water በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ አሳትሞ አውጥቷል። ይህን የአል ላባድን መጽሐፍ “አስ ሳፊር” የተባለ የሊባኖስ ዕለታዊውና ተነባቢ የዐረብኛ ጋዜጣ የመጽሐፉን አጭር ዳሰሳ በፊት ለፊት ገጹ ይዞ ወጥቶ ነበር።