ሙገር ሲሚንቶና ሲቪል አቪዬሽን በሕገወጥ ግብይት ሪፖርት ቀረበባቸው

– ሦስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል

ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ የሲሚንቶ ሽያጭና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የግዥ አፈጻጸም ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ ተደጋጋሚ ችግሮችና ክፍተቶች የሚታይባቸው መሆኑን፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡