በጥያቄዎች የተከበበው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ መመርያ

ሰሞኑን የወጣውን የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን መመርያ ተከትሎ የንግድ ማኅበረሰቡ ግራ እየተጋባ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን የሁሉም ነጋዴዎች አስተያየት ተመሳሳይ ባይሆንም ሪፖርተር ያናገራቸው የንግዱ ማኅበረሰብ አካላት ግን በሁለት የተራራቁ ግን ተመሳሳይ የችግር ማዕቀፎች ውስጥ ይወድቃሉ፡፡