ሁለ ገብ ትግሉና ህዝባዊ አመጽ። ዛሬስ። ከዳኮታ የጥናት ማእከል።
ያፍሪካ አንድነት ሀምሳኛ አመት ክብረ በአል በአዲስ አበባ በፈረንጆች አቆጣጠር may 25 2013 የካሄዳል። ብዙ አፍሪካና የሌሎች አገር መሪዎች ትላልቅ ባለስልጣናትና ዲብሎማቶች ይገኛሉ። ብዙ የውጪ አገር ጋዜጠኞች ለበአሉ አዲስ ይገባሉ። ጊዜው አጭር ነው ልናደርግ የምንችለው ነግር ይኖር ይሆን?። ደደቦች ነን ቀድመን ሊታሰበን ባለመቻሉ።
ይህ ጽሁፍ መታሰቢያነቱ ለአንዷለም አራጌ፤ ለስክንድር ነጋና ለኛ ሲሉ በወያኔ እስር ቤት ለሚማቅቁ ወገኖቻችን ይሁን።
ሁለገብ ትግል የሚለው ጽንሰ ሀሳብ የህዝባዊ አመጽ( አቢዬት) በዋናነት ታሳቢ ያደረገና ያካተተ ነው። ይህ ዛሬም የብዙ ድርጅቶች የትግል መርህ ነው። ይህ አቋም በድርጅቶች የተያዘው የአረቡ አቢዮት ከመጀመሩ አይደልም ከመታሰቡ በፊት ነው። ከአገራችንና ካለንበት ሁለንተናዊ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተንተርሰው የሚሰራ መሆኑን አስበውበት የያዙት አቋም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ይህ አቋም ህዝብ እንቢኝ ለማለትና ለማመጽ በዋናነት አብዛኝው ህዝብ በጭቆናና በአፈና ስር መኖር አለበት ከሚለው ትክክለኛ መሰረት ላይ የተነሳ ነበር።
ለየት ባለ ሁኔታ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን አይን ባወጣ አድሎ፤ ዘርኝነትና መበዝበዝ ውስጥ እንኖራለን። የምንታገለው ሀይል በወረቀት ላይ ባለና በታቀደ መንገድ በተደጋጋሚ አንድነታችንን ለመናድና በሉአላዊነታችን ላይ ጉዳት ያደረሰ ወደፊትም የሚያደርስ መሆኑን ለአቅመ አዳም የደረሰ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በሚያውቅበት ሁኔታ የሚደረግ የህዝባዊ እንቢተኛነት ትግል ነው። የማያነብና የማይሰማ እስከጭራሹኑ የአገሩን ጠቅላላ ሁኔታ የማይከታታል ዜጋ ቢኖር እንኳ አይኑም ልቦናውም ከአልታወረ ያገራችን ካርታ አሁንና በፊት ምን እንደሚመስል የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም።
ትግላችን ዜጎች በሙሉ ሊሰኝ በሚችል በጣም በጣም ብዙዎቻችን ከጥቂቶች ጋር የምናደረግው ነው። በእርግጥ አሁን ሁላችንም ድርሻ እያደረግንበት ያለ ትግል አይደለም። ሁላችንም ወይም የበዛነው የድርሻችንን ማድረግ ስንጀምር ለመደቆስ ክርናችን ይጠነክራል። ያኔ ከጥቂቶች ውስጥም አንድ ሁለት ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ እሰከመጨረሻው ሊገዳደሩን የሚችሉበት እውነት የማያከራክር የትግሉ ባህሪ ነው።
በርግጥ በተለያዩ ምክንያቶች ይህን እአደገኛና አስፈሪ ሁኔታ ለምለወጥ በሚደረገው ጥረት ምንም አስተዋጾ ለማድረግ የማይፈልጉ አሉ። ያም ሆኖ ከዚህ ክፍል ውስጥም ሁሉም እስከመጨረሻው ከዋናዎቹ ተፈራጆች ጋር አብረው የሚታገሉ ናቸው ማለት አይደለም። ቁጥሩ ክዚህ ክፍል እጅጉን የበዛ ደግሞ ዛሬ ሲንገበገብ የሚኖርና ትግሉ ላይ ንቁ ተሳታፊ ነው። ከዚህኛው ቁጥር የበዛው ደግሞ በራሱ ተነሳሽነት ሳይኖረው ቀርቶ ለጊዜው የድርሻውን እያደረገ ባይሆንም በአግባቡ ከተደረሰ ዛሬ የድርሻውን ለማድረግ አሳምሮ የሚፈልግ ነው። ከስካሁን ከገራችን የትግል ተሞክሮም ሆነ የህዝባዊ እንቢተኛነት ከተደረገባቸው አገሮች ልምድ ትግሉን ስራዬ ብለን የያዝነው በግባቡ ልናካሂደው ስንጀምር የበዛው በሂደት ትግሉን እንደሚቀላቀል በርግጠኛነት መናገርም ይቻላል ።
ምስጋና ለአረቡ አለም አቢዬት ህዝባዊ እንቢተኛነት ከድርጅቶች አልፎ ብዙ ቁጥር በአላቸው ዜጎች ዘንድ እንደ አንድ አይነት የትግል አማራጭ ተድርጎ የሚታይ ነው። እንዲያድግ ሆኖ በአገራችን የተተከለ ችግኝ ነው ማለትም ይቻላል። የችግኙ የእድገት ፍጥነት ግን የምንታገለው አካልና እኛ ለችግኙ እንደምናደርግለት እንክብካቤ የሚወሰን ነው የሆነው። እኛ መኮትኮትና ውሃ ማጠጣቱን ስራዬ ብለን አልያዝነውም። ጥሩነቱ ወያኔዎች ግን መንከባከቡን አላቆሙም። በተጨማሪም አሁን እየደበዘዘ ቢመጣም በጊዜው በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ይህ አይነቱ የትግል አይነት ይሰራልና አሁን የሚቻል አይደለም በሚል ይደረግ የነበረው ውይይት በተመሳሳይ ይህንን አይነቱን ትግል በማስተዋወቅ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል። በርግጥ ውይይቱ አሉታዊሚ አወንታዊም አስተዋፆ ነበረው።
1- ትግሉ በተደረገባቸው አገሮች ውስጥ የነበረው ነባራዊ ሁኔታዎች የተለያዩ ሆኖ እያለም እኛ እንጠቀምበት ዘንድ የግድ ከአንዱ አገር ጋር ሙሉ በሙሉ መመሳሰል አለበት ከሚል ስሌት በመነሳት የማመሳሰል ስራ ነበር።
2- ለምንታገለው ክፍል ጥንካሬ ያልሆኑ ነገሮችን ጥንካሬ አድርጎ ማቅረብ ነበረበት።
ለምሳሌ፤- ሁለት መቶ ሺ አካባቢ የሚቆጠር ከህዝብ የወጣ ሰራዊት በአንድ ዘር ጠቅላላ አመራር ስር መደራጀቱ ጥንካሬ ሆኖ ቀርቧል። ያንድ ዘር የበላይነት በገነነበት አድሎ ጣሪያ በነካበት ወያኔ ከፋፍሎናል ምክንያት ነበር። እነዚህ ጥንካሬ ሊሆን የሚችሉት አግባብ ያለው ስራ እስከጭራሹ ሳንሰራባቸው ወደ ህዝባዊ አመጹ ከገባን ብቻ ነው። ያውም ምን አልባት። እንዲሁ መግደል ማሰርና፤ ማሰደድ ጥንካሬ ሆኖ ተወስዷል። በጅምላ በመግደልና በማሰር መንግሱትን ያፀና ያለ ይመስል።
3- ያስፈልጉናል ጎደሉ ተብለው ሲጠቀሱ የነበሩ ቁም ነገሮች ነበሩ።
የተባበረ ተቃዋሚ፤ ሜዲያ፤ የተደራጀ ሀይል፤ መሳርያ የታጠቀ ሀይል፤ ሽግግሩን ያአገሪቷን ሉአላዊነት አደጋ የማይጥልና ሁከት ያልበዛበት ማድረግያ ብለሀት፤ ቁርጠኝነት ያለው ታጋይ…. የመሳሰሉትን ማስታወስ ይቻላል።
ብዙዎቹ በርግጥም የሚያስፈልጉን ናቸው። ችግሩ ከአልተሟሉ አይቻልም ከሚል አቋምና ይባስም ብሎ እስከጭራሹ ተሰርተው ሊሟሉ የማይችሉ አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ ነበራቸው። በዚህ ምክንያት ህዝባዊ እንቢታው ላይ የነበረውን የትግል መነሳሳት ላይ አፍራሽ ሚና ከመጫወትም አልፎ ያስፈልጉናል የተባሉት ጉዳዮች ጠንክረን እንዳንሰራባቸው አድርጓል። አንዳንዴ መከራከሪያዎቹ አገርን ያነሰ ከመውደድና፤ ህዝብን ከማስጨረስ ጋር ተያይዞ ይቀርብ ስለነበር በጊዜው ዳር ዳር ያሉትም ህዝባዊ እንቢታውን ትግል በሙሉ ልብ አጠንክረው ሊገፋበት አልቻሉም። በተወጠረ ገመድ ላይ ዱላ ይዘው የሚሄዱ ነበር የሚመስሉት። ያም ሆኖ ግን ዛሬም ቢሆን የጎደሉትን ለማሟላት የሚፈጨረጨሩት ህዝባዊ አመጽን እንሞክረው የሚል አዝማሚያ የነበራቸው አካላት ናቸው። ይህ በራሱ ብዙ ይናገራል።
እሰከሰራንበትና ተሰርቶ ይመጣል በሚል ከሆነ ለወደፊቱም አልተሟላምና በበቂ አልተሰራበትም የሚለው ጉዳት የለውም። የአረቡ አቢዮት ከተካሄደባቸው አገሮች ጋር በንጽጽር ስናየው ግን። እኛ ዛሬ ያለንን የሚያህል የተደራጀ ተቃዋሚ ሆነ መዋቅራዊ ጥንካሬ ያላቸው ድርጅቶች አንዳቸውም አልነበራቸውም። የኛዎቹ ተዋህደው አንድ ባይሆኑም ፖለቲካው ሲተነትኑ እንጂ ጥቃትና ጥፋት በአገርና በህዝብ ላይ ሲፈጸም፤ ተባብሮ ለመታገልም ሆነ ስራን የመስራት ችግር አይታይም። እንደውም ተባብሮ መታገሉም ሆነ መስራቱ ከጊዜ ጊዜ በጣም እየተሻሻለ ነው። ትብብርን በሚመለከት መሰባሰቦች አሉ። ቡዙ የተባለበትና የበሰለ ጉዳይ ስለሆነ ግድ ሲል ያሉት ድርጅቶች በቀላሉ አንድ ሆነው ይታገላሉ ብሎ ደፍሮ መናገር ይቻላል። ዛሬ አንድ አላደርግ ያሉን የተራራቁ አቋሞችና አቋሞች በጣም በጣም ተጠጋግተዋል። በአጠቃላይ ህዝባዊ አመጽ ከተካሄደባቸው አገራት ያኔ አይደለም ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ያልቻሉት ይበዛሉ።
ሁሉም መሳርያ የታጠቀና አስፈላጊ ሲሆን ከህዝብ ጎን የሚቆም ሀይል አልነበራቸውም። የነበራቸውም ዛሬ እኛ ካለን ያን ያህል ጠንካራ ነበር ለማለት የሚቻል አይደለም። በተመሳሳይ ካሸነፍን በሗላስ፤ መሸጋገርያው ምን መምሰል አለብተ፤ አገር ማረጋጋት የሚሉት ጉዳዮች ላይ እኛ ዛሬ ያለንን ጠቅላላ ግንዛቤና ዝግጀት አመጹን ሲጀምሩት አንዳቸውም አልነበራቸውም። እንደውም ያሰቡበትም አይመስልም። የብዙዎቹ በውጪ ሀገራት ድጋፍ በመከራ የተጠጋገነ ነው ዛሬም ያለው። በርግጥ የመገናኛ መኖርና ዘመኑ ያፈራውን መገናኛ በመጠቀም ከኛ በጣም በጣም የተሻሉ ነበሩ። እኛ በቀላሉ የማናገኘው ወይ እስከጭራሹ የማናገኘው የሌሎች አገሮች ድጋፍ ነበራቸው። ስለዚህም በቀላሉ የበዛ የአለማቀፋዊ መገናኛ ሽፋን አግኝተዋል።
ሀ- ስለመገናኛ።
ህዝባዊ አመጹን ለማካሄድ ካሉብን መሰረታዊ ችግሮች አንድ በርግጥም በቂ መገናኛ አለመኖር ነው። ችግሩ ግን በቂ መገናኛ አለመኖሩ ብቻ አይደለም። ያሉንንም ትግላችንን በሚያግዝና በሚያፈጥን መንገድ መጠቀም አለመቻላችንም ሌላው ችግር ነው። እንደ አባይ ወንዝ ወራጅነቱ የማይቋረጠው ወያኔ የሚፈጽመውን ግድያ ፤ ማሰቃየት፤ ግፍ፤ ማፈናቀልና እንግልቶች የበዛውን የመገናኛ አውታሮቻችንን ሽፋን ወስዷል። ጥራዝ ነጠቆችና የወያኔ በአለስልጣናት እንዳበደ ውሻ በአሰኛቸው ጊዜ እየወጡ ለሚወረውሩት ሀሳብ ሁሉ ማረሚያና ማስተማርያ የሚሆን መልስ መስጠት እንዲሁ ቀላል የማይባል ሽፋን ይወስዳል። በአጠቃላይ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ህዝብን ለትግል ማዘጋጀቱ ላይ የተሰጠው ትኩረት ለቲካ ቲካ ከሰጠነው ሽፋን በጣም ያነሰ ነው።
ይህን የምንለው በተናጠል የሉንን የመገናኛ አውታሮች ተመልክቶ ግን ይደለም። አንዳንዶች ከሌሎች የሚሻሉበት ሁኔታ አለ። አንዳንዶች ለምን በዚህ መንገድ እንደሚሰሩም ግልጽ ነው። ዘመኑ የፈጠራቸው መገናኛዎችና የድርጅት ራዲዮ ጣቢያዎች በቀጥታ ትግሉ ላይ የማያወሩበት ወይ የማታገያ ጣቢያ የማይሆኑበት ምክንያት ግን የለም። ዋናው ችግር ግን የመገናኛዎች ብቻ አይደለም ትግሉ ላይ በየዘርፉ ምን መደረግ አለበት የሚለው ላይ ሊናገሩና የሚያስተምሩ ጠበበት አለመኖር ነው። ወደህዝባዊ አመጽ ከመግባታችን በፊት ህዘብን ለትግል የማዘጋጁና የለውጥ ግብር ሀይል በየዘርፉ ማዘጋጀት የሚችሉ ጠበብት እጅጉን ያስፈልጉናል።
እንቢተኛነቱ ከመጀመሩ በፊት ቀድሞ ሁሉም የድርሻውን ማወቅ፤ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሚያደርገውን፤ መውሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ፤ እንቢተኛነቱን የሚያደርግበትን ስረአት ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። ይህ አካሄድ ከአለንበት መጠነ ሰፊ አፈና አኳያ ለመደራጀት ላሉብን ከባድ የሆኑ ችግርም መለስተኛ መፍትሄ አድርገን ልንጠቀምበት እንችላለን። መገናኛን በሚመለከት እርቀን ተጉዘንም አንዴ እንቢተኛነቱን ከጀመርን በሀላ ሊኖር የሚችል የግንኙነት መታወክ ድረስ ልናስብበት ይገባል። በኛ በኩል መፍትሄ ብለን ነጻነታችን ላይ የሚንቀለቀል ፍላጎታችንና ጥልቅ ስሜታችንን የመጠቀም አስፈላጊነት ድረስ ወስደንዋል። መናበብን ያመጣንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነበር።
በየሜዲያዉ በጽሁፍም በንግግርም አስተዋጾ የሚያደርጉ ዜጎች ጥቂቶች ናቸው። ከእነዚህም የበዙት በቀጥታ ትግሉ ላይ አተኩርው አይሰሩም። ሌላው ህዝባዊ እንቢተኛነቱን ለማስተባበር ሀላፊነት የወሰዱና ቁጥራቸው ቀላል ማይባል የሰቪክ ማህበራት የለውጥ ሀይሉን ማዘጋጀቱን አላማ አድርገው ትግሉን በሚያፋጥንና በሚጠቅም መንገድ ሜዲያዎችን መጠቀም አይሞክሩም። እነዝህን የመሳሰሉ ችግሮች ሜዲያዎቻችን አታጋይ እንዳይሆኑ በጅጉ አድርጓል። አሁንም ቢሆን ነገ ህዝብ ማወቅ ያለበትን ቀድሞ ዛሬ ይወቅ። መሰማቱን እርግጠኛ ለመሆን ቀድመን አሁን መጀመር ብቻ ሳይሆን ተደጋግሞ ይነገር።
መደራጀትን በሚመለከት ከመገናኛ አጠቃቀም ጋር አያይዘን የያንበትን ጉዳይ ሰፋ ለማድረግ። ለሁላችንም የመደራጀት አስፈላጊነት አያከራክርም። ጥያቄው ትግሉን አሸናፊ ለማድረግ ምን ያህል ዜጋ በድርጀት ማእቀፍ ውስጥ ማዘጋጀት አለብን የሚለው ነው?። ይህ ከታወቀ በአገር ቤት ለትግሉ የሚያስፈልገውን የሰው ህይል ለማደራጀት ከአለብን ችግር አኳያ ማደራጀት ከሚገባን አንድ ሶስተኛውን በማደራጀት የቀረውን ሶስት እጥፍ ቀድሞ ባወቀና በገባው ታጋይ ሀይል ልንሸፍነው የምንችልበት ሁኔታ አማራጭ ሊሆን ይቻላል የሚል ግምት አለን። በርግጥ በተያያዥም ማደራጀት የተቻለውን ከፍል ሙሉ አስተዋጾ በአግባቡ መጠቀም ምን አልባትም መስራት ከሚገባው በላይ እጥፍ ማሰራትም አብሮ ሊታሰብበት ይገባዋል።
ጠበብት ስንል፤- በየክፍሉ የጠለቀ እውቀቱ ያለው ካለ እሰየው። ከሌለ እራሳችንን ምሳሌ በማድረግ ብዙዎቻችን ልናደርገው ስለምንችል መድፈር ያለበትና መታረም የሚችል መሆኑን አውቆ አንድን አርእስት ስራዬ ብሎ ይዞ፤ የተቻለውን ያህል አርስቱ ላይ አንብቦ ፤ ጊዜ ሰጥቶ በይበልጥም ተብሰልሰሎ፤ ከኛ አገር ሁኔታና አቅማችን ጋር በተቻለ አስማምቶ ትግሉ ላይ ስለሚደረግ አስተዋፆ ነው።
ማስተማር ስንል ፤- በአለው ግዙፍ አፈና ውስጥ እራሳችንን ስለማደራጀት፤ ወይ መረጃን እንዴት እንደምንለዋወጥ፤ ዘምን ያመጣቸውን መገናኛዎች ትግሉ ላይ አጠቃቀም። ትግሉ ላይ መነቃቃትን መፍጠር ስለሚቻልባቸው መላዎች። ተማሪው፤ ኦፒዲዎው፤ ወላይታው፤ ወታደሩ፤ ቤንጤ ቆስጣሉ አይነት የዜጎችን ድርሻ በየማህበረሰባዊ ስብስቡ ምን አስተዋፆ ማድረግ እንደሚችል ማሳየትን ያካትታል። ትግልን ስለማቀናጀት ወይ ትግሉን ህዝባዊ ለማድረግና ስለቃላት አመራረጥ ሊሆን ይችላል።
ኢሳትን በሚመለከት፤-ጠንካራ የሆነ አማራጭ መገናኛ ማቆም ወሳኝ ነበር። ምስጋና ላስቻሉት ተችሏል። ኢሳት ያለን አንድ ነገር ነው።በጣም ጥሩም እየሰራና ያማራጭ ሜዲያ አገልግሎት እየሰጠ ነው። ስራውን የሚሰሩት ድቅድቅ ባለ አፈናና ዝግ በሆነ አገር ውስጥ ለዛውም በርቀት ሆነው ነው። በአፈናውና በርቀቱ ምክንያት የጠራ መረጃን ለማግኘት የሚኖረውን ችግር ጥሩ አሳቢ የሆነ ሁሉ መገመት አያዳግተውም የሚል እምነት አለን። ያም ሆኖ የጠራና እውነትነት ያለውን መረጃ ለህዝብ ለማቅረብ አዘጋጆቹ ምን ያህል እንደሚጥሩና ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ዝግጅቶቹን ለሚከታተል ሁሉ በደንብ ይታያል። አስገራሚ በሆነ ሁኔታ እስካሁን ተሳክቶላቸው የሚቀርቡት ዝግጅቶች የጠሩና እውነትነት ያላቸው ናቸው። ላንድ መገናኛ ወሳኙና ዋናው ይህ ነው። በተጨማሪም ኢሳት ትግሉ ላይ እያበረከተ ያለው አስተዋጾ ግዙፍ ነው። ስለዚህም ኢሳትን ላይ መረባረብም ልንጠነቀቅለትም ያስፈልጋል። ለኛ ከምንኖርበት ጭቆናና ዘግናኝ በደል አኳያ ትግል ላይ እንዳለ ዜጋ ከተለመደው የመገናኛ አገልግሎት ለየት ባለ በከፊልም ቢሆን በቀጥታ የማታገያ መሳርያም መሆን አለበት ስለምንል አልፎ አልፎ የሚቀርቡት ትችቶች በሙሉ ቅምም አላደረጉንም። የበዙት የቅንጦት ናቸው፤ ሌሎቹ እውነትነት የሌላቸው የቀሩት የተንሸዋረሩ ሆነው ነው ያገኘናቸው።
ለ- የውጪውን አለም ድጋፍ ስለማግኘት።
አውጥተን ስለማንናገረው ነው እንጂ በዋናነት ያደግን ብለው እራሳቸውን ከሚጠሩት አገሮች መንግስታት ላይ ያለን ቅሬታ ለምን ይህን አየነት ግፍና በደል ሲፈጸምብን እያዩ አይረዱንም አይደለም። ለገዳዮቻችና ለጨቋኞቻችን ሙሉ እርዳታ እንደሚያደርጉ ስለምናውቅ ነው። ጥሩነቱ በነዚህ አገራት እጅግ ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንኖራለን። እንዴት የሚለውን ዝርዝር እዚህ መናገር አያስፈልግም። እንደ ህዝባዊ እንቢታው እንደሚካሄድበት ሁኔታ ብዛታችንና ልምዳችንን ተጠቅመን እርዳታቸውን እንዲያቆሙ አልፎም ከኛ ወገን እንዲሆኑ ማስገደድ ድረስ ለመሄድ ግን አቅሙ አለን። የመጨረሻው ደረጃ ድረስ ወስደነው ወገናችን በገፍ ሲጨፈጨፍ እያየን ዝም አንልም። በገፍ መታሰር ከሆነ የሚፈልገው በገፍ እንዲያስሩን እንገፋቸዋለን። ሞታችን ከሆነ የሚያሰማን መግደል እሲከጀምሩ ድረስ በያለንበት እናምጻለን። ለመሰማት እራሳችንን መጉዳት ካለብን መጉዳት ድረስ መሄድ አማራጭ እንዳለን ማወቅ አለብን።
በተያያዥ በውጪ አገራት የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ በተመለከተ ብዙ የሚባሉ ነገሮች አሉ። ተመችቶት በርገር እየገመጠ የሚኖር። ያገሪቷን ተጨባጭ ሁኔታ የልተረዳ፤ ወጪ ሆኖ አገር ቤት ባሉ ወገኖቹ መሰዋትነት ነጻነትን ማግኘት የሚፈልግ። አገር ውስጥ የሚካሄደው ትግል አሽከርካሪ መሆን የሚፈልግ፤ ትግሉን አጋዥ ብቻ ነው መሆን የሚችለው። እንደውም ሊያደርግ የሚችለው አስተዋፆ ተገድቦ በገንዘብ መርዳትና በዲፕሎማሲው ትግል ዘርፍ ብቻ ነው የመሳሰሉ። ዋናው ምንጫቸው የታወቀ ነው። ያም ሆኖ በውጪም በውስጥም ትግሉ ውስጥ ያሉ ወገኖችም ተመሳሳይነት ያላቸውን ሀሳቦች ሲጋሩ ይሰማል።
በሰፊው አንሄድበትም። ልንከራከርበት እንችላለን በኛ እይታ ግን አንዳቸውም እውነትነት የላቸውም። እነዝህ አይነት ገለጣዎች በውጪ አገራት የሚኖረውን ላገሩ ቀናዊ የሆነ ኢትዮጵያዊ በፍፁም አይገልፁትም። አገር ቤት እያሉ ትግሉ ላይ የድርሻቸውን ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ወጥተውም ትግሉ ውስጥ እንደምናገኛቸው። በተመሳሳይ በውጪ ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ገብተው በቀጥታ ትግሉ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ብዙ አስረጅ መጥራት ይቻላል። በውጪ የሚኖረው እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ከቆረጠ በቀጥታ ገብቶ የትኛውም አይነት ትግል ላይ መሳተፍ አሁንም የቻላል። እያደረጉትም ያሉ አሉ።
በዛሬው ጊዜ ከበምንኖርበት የመገናኛ ቴክኖሎጂ አኳያ አንድ ወገናችሁ ውጪ ስለሚኖር ከቆረጠ ያገር ቤቱ ትግል ላይ ላያበርክት የማይችላቸው ጉዳዮች በጣም ትንሽ ናቸው። ማደራጀት ይችላል፤ ማንቃት ይችላል፤ መረጃ መሰብሰብና መልሶ ማቀበል ይችላል። መቦርበር፤ ጠላትን መከፋፈል ይችላል። አገር ቤት ባለው አፈና ምክንያት ምን አልባትም አገር ውስጥ ካላችሁት የትግል አጋሮቹ በተሻለ። አንዳንዴ መሰዋትነቱ ይለያይ ይሆናል እንጂ ሁሉም ግን ያለ መሰዋትነት የሚደረግ ትግል አይደለም። ምክንያቱም ንፁህ አገርና ህዝቡን መውደዱ ብቻ ነው። እንደውም በውጪ ያለው ዜጋ እርቆ እንደመኖሩ እኔን በቀጥታ ስለማያገኘኝ አለማለቱም ምንአልባትም ጥሩ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያሳይ ነው።
4- መሰዋትነት ሳይኖረው መደረግ አለበት።
ትግል የሌለበት የሰው ልጅ ታሪክ አልነበረም። በአለም ላይ እስከዛሬም ትግል የማይካሄድበት አገርም የለም። የመሰዋትነቱ አይነት ይለያያል እንጂ መሰዋትነት የሌለውም የትግል አይነትም የለም። ሁሌም ቢሆን ትግል የማይኖርባት ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልምና በዚህ አይነት ቅዠት ውስጥ ዛሬም ላላን ይቁረጥ። በርግጥ የኛ ትግል መሰረታዊ ነው። የተለየ ሀሳብ ማራመድ ያስገድላል። መጻፍ መናገር መቃወም ሁሉም ነገረ ሊያስገድል ወይ እዴሜ ልክ ያሳስራል። በዚህ አይነት አገር ውስጥ እየኖርን ዛሬ ገለለተኛ ነን የምንለውም ቢሆን በኛ ሲመጣ ነገ መቃወማችን አይቀርም። ሰውነንና የተለየ ሀሳብ ይኖረናል፤ የማንስማማበት፤ የማንጠቀምበት ወይ ምንጎዳበት ጉዳይ መፈጠሩ አይቀርም። ስለዚህም ዛሬ የሚደረገው ትግል በተቃወምን ቁጥር የማያስገድለን የማያሳስረን በኣጠቃላይ የከፋ መሰዋትነት የማያስከፍለን አገር ለመፍጠር መሆኑን ማወቅ አለብን።
አወዳድረን መሰዋት ስለመሆን የምናወራ ከሆነ እናስላው። የህዝባዊ እንቢተኛነት ትግል ላይ ትኩረት ሰጥተን ማውረቀት ከጀመርን በሗላ ብቻ እንኳ የተከፈለው መሰዋትነት እጅግ ብዙ ነው። ብዙዎች ተገለዋል፤ ብዙዎች ዛሬም ድረስ በእስር እየማቀቁ ነው። በዙዎች ተፈናቅለዋል፤ ብዙዎች አገራቸውን ለቀው መከራ እንዲያዩ ተዳርገዋል። ዜጎች በዘራቸው ምክንያት አገር እያላቸው አገር አልባ እየሆኑ ነው። አገራችን በትግሬ ወያኔዎች ስር እስካለች አይደለም ሌላው አይነት መብት እንደየ እምነታችን በሰላም ፅሎታችንን አድርገን መኖር የማንችልባት ናት።
በተደራጀና መስመር በያዘ መንገድ ሁላችን ትግሉን በጊዜው የሚያስከፈለውን መሰዋትነት ያስከፍል ብለን አድርገነውስ ቢሆንስ ወይ ህዝባዊ አመጹ ላይ እየሰራንበት ቆይተንስ ቢሆን?። ይሄኔ ነጻነታችንን አውጀን ነበር። በዛ ላይ መሰዋትነቱ የፈራነውን ያህል ከባድ ላይሆንም ይችላል። አንዴ የሚያስከፍለውን መሰዋትነት መክፈል ወይ ጨፍጫፊዎችና አረመኔዎች በነገሱበት አገር የዜጎች መገዳደርም ሆነ መሰዋትነቱ ኡደት ነውና ሁለቱም መቀጠሉ አልቀረም። ጥያቄው ይቀጥል ወይ የሚል ነው?። ይቀጥል ካላልን ይገላሉ በሚል ሰበብ ፈቅደን የንጽሀንን ፍጅትና እንግልት እየቆጠርን እንኑር ወደሚል ድምዳሜ የሚያደረስ አይሆንም ወይ?።
በተጨማሪም ህዝባዊ እንቢተኛነቱን በሚመለከት መግደልና ማሰራቸው ሁለት ጎኑ ስለታም የሆነ ቢላም ሊሆን ይችላል። ጭንብል ለባሽ አሸባሪዎችን ማሰወገድን እርግጠኛ ግብ አድርገን በህብረትና በማወቅ ከገባንበት የትግል ጓደኞቻችን መሰዋትነት ያጸናናል ያበዛናል ቁርጠኛ ያደረገናል። ወደፊት እንጂ ወደሗላ እንድንል በጭራሽ አያደርገንም። ያኔ ስለቱ ወደነሱ አብዝቶ መገዝገዝ ይጀምራል። መግደልና ማሰር ለህዝባዊ እንቢታው የጥንካሬ ምንጭ እንጂ ለምንታገላቸው ሀይሎች ጥንካሬ ሁሌ ሊሆን አይችልም።
መግደል ማሰርና ህዝባዊ እንቢተኛነትን በሚመለከት ከሚሰጡት ምክንያቶች አሳማኝ ቁምነግሮችም በርግጥ ነበሩ አሁንም አሉ።
– ሰላማዊና ህጋዊ መሆን አለበት። ትክክል ህዝባዊ እንቢተኛነት ሰላማዊና ህጋዊ ትግል ነው። ገፍተው ከግድያ አልፈው ወደ ጅምላ ፍጅት እስኪያሳድጉትና ወደመከላከሉ እስካልገፉን ድረስ። የገደሏቸውን አንጀታችን እያረረ በክብር በዝተን እየወጣን እየቀበርን የበዛ ትግስትና ጨዋነት ባለበት ለረጅም ጊዜ የምናስኬደው ትግል ነው የሚሆነው።
– መሰዋትነቱን ማሰቀረት አለመቻሉ ታሳቢ ሆኖ ማሳናስ የሚቻልባቸው ስራዎች ሁሉ ቀድመው መሰራትና አማራጮች ሁሉ ላይ ጊዜ ተሰጥቶ ሊታሰብበት ይገባል። ይህም ሁሌም ትክክል ነው። በረግጥም ይህን ማድረግ ይቻላል። መንገዶቹም አሉ።
– ከዚህ በሗላ የተነሳንበትን ከፍጻሜ ሳናደርስ ማቆሙ ጉዳት አለው። የምንታገላቸው ጭንብል ለባሽ መደዴዎች ናቸውና እራስን ከመከላከል አኳያም ሆነ ከታሰበው ግብ ያለጥርጥር ለመድረስ እንደነሱ በተመሳሳይ መሳርያ የያዘ ሀይል ማቆም አለብን የሚለውም ትክክለኛነት አለው። እዚህኛው ቁምነገር ላይ በርግጥ ጅማሮው ጥረቱም አለ። በቂ ርብርቦሽ ግን ዛሬም አይታይም። ህዝባዊ እንቢተኛነቱና እራስን መከላከል በተመለከተ ግን የተላያየ ደረጃዎችና ባህሪያት እንዳሉት ከዚህ ጋር አብሮ መታየት አለበት።
የመጀመርያው ደረጃ ፍጽም ሰላማዊ ህገመንግስታዊም ትግል ነው። ብብዙ ቁጥር እየተሳተፍን ቀላላ ከሆኑ እንቢታዎች የሚጀምር ነው። ከላይ እንዳነሳነው የሚያስሯቸውን እንዲፈቱ እየጠየቅን፤ የገደሏቸውን ጥርሳችንን ነክሰን በዝተን በመቅበር ጥብቅ በሆነ ትእግስትና ስረአት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የምናካሂደው ነው።
ከአንደኛው ወደ ሚቀጥለው መሸጋገሩ እነሱ ከሚወድሱት እረምጃ ጋር የተያያዘ ነው። ቀጣይ የሚሆነው ሰረአት አልበኛነታቸውና ጭካኔያቸው በርትቶ የሚገድሏቸውና የሚያስሯቸው ንጽሀን ጓዶቻችን ቁጥር በመቶዎችና በሺዎች መቆጠር የሚጀምርበት ጊዜ ስንደርስ ነው። በዚህ ጊዜ ጩህት፤ እልህና ንዴት ከሁሉም አቅታጫ አየሩን ይሞላዋል። ይህ የሚታይና የሚጨበጥ ስሜት ይሆናል። ያኔ ፍረሀት ቦታ አይኖረውም። እኛ በጣም እየበዛን ስንሄድ እነሱ እያነሱና እየተመናመኑ ይሄዳሉ። አመጻችን በአይነቱም በጥንካሬው ያድጋል። እስከዚህ ድርስ በተቻለ መጠን እንቢታችን ሰላማዊ የሚሰኝ ሆና የሚቀጥል ነው የሚሆነው። መግደሉም ሆነ ማሰሩን ግን ያለ ከፍተኛ ቁጣና አመጽ በቀላሉ ሊያደርጉት የሚቻላቸው አናደርግላቸውም። መቋቋማቸው ከዚሀም ላያልፍ፤ ፍጻሜያቸውም እዚህ ደረጃ ሊሆን ይችላል። በተቻለ መጠን ሁለተኛው ደረጃ ላይ በመሳርያ እራስን ወደመከለካል ሳንሄድ ረዘም ላለ ጊዜ መያዙ ሊጠቅመን ይችላልና በአንክሮ ሊታይ ይገባዋል። መሳርያ የያዘ አካል ስላልነበራቸው በጀመሩት ሰላማዊ አመጽ መጽናት ግድ የሆነባቸው አገራት ተጠቃሚ የሆኑበት አጋጣሚ አለ።
ከዚህም አልፈው ወደ ሶስተኛው ደረጃ ገፍተው መሄድ ከወሰኑ በታዛዥነታቸው ፀንተው አብረዋቸው ያሉትን ይዘው ፍጅት ጀምረዋል ማለት ነው። ነጻነታችንን ለማግኘት በዚህ ውስጥም ማለፍ ካለብን እናልፈዋለን ሌላ አማራጭ የለንም። ያኔ ውሻም ሆነ ሰው የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ላይ መተኮስ ስለሚጀምሩ የአመጹ የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደደረስን ይገባናል። በዚህ ጊዜ ላለመገደልና ላለመያዝ መከላከል አማራጭ መሆኑን ሁሉም ይረዳዋል። በርግጥም መከላከሉ መብትም፤ ተፈጥሯዊም ነው። የሰው ልጅ ባይሰለጥንም፤መሳርያም ባይኖረው በጁም በጥርሱም በዶማውም ለመኖር ሲል ይተናናቃል። ሁሉም አካባቢውን ከጭንብል ለባሽ ጨፍጫፊዎች ቢያጸዳ ኢትዮጵያችን ትፀዳለች ድረስ ይሄዳል። ያኔ አካባቢህን አጽዳ፤ ጎረቤትህን እርዳ ነው መፈክሩ የሚሆነው። እዚህ ደረጃ ላይ ስነደርስ ከህዝብ ጎን የሚቆምና መከታ ሊሆን የሚችል የታጠቀና የተደራጀ ሀይል መኖሩ አስፈላጊነቱ አሌ የማይባል ነው። ይህን ማዘጋጀቱ የራሱ ብዙ ችግሮች ሰላሉት ህዝብ እራሱን የሚከላከልበትን መሳርያ ማቅረብ የሚቻልበትን ደረጃ ድረስ መዘጋጀት ከተቻለም ቀላል አይደለም። ስለዚህ ልንረባረብበት የሚገባ ነው።
በአጠቃላይ በህዝባዊ አመጽ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ሊፈጠሩ የሚችሉ ነገሮች ላይ የተጠጋ ግምት አሁን ማስቀመጡ ጠቃሚ ነው። በተቻል መጠን የበዛው ህዝብ በተገቢው ሁኔታውን በተረዳበት አመጹን መጀመር ጥሩ ነው። ይህን ማድረጎ ትግሉን አሸናፊ ለማድረግና ስጋቶቻችን ላይ መፍትሄ ቀድሞ ከመስራት አኳያ የራሱ አስተዋጾ አለው። በርግጥ ግምቱ ሰፊና ጥልቅ መሆን አለበት። ሚዛናዊ መሆን አለበት። በኛ በኩል ያለውን ስጋትና አደጋ ብቻ ሳይሆን በምንታገላቸው ክፍሎች በኩል ሊሆን የሚችለውን ባካተተ ተደጋግሞ ቢባልበት ጥሩ ነው።
የአረቡ አቢዮት ከጀመረበትና ይህን አይነቱ የትግል አይነት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አማራጭ መታየት ከጀመረ በብዙ መልኩ ያገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተቀይሯል። ምን አልባት ጊዜው ይሆን ወይ?። የስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ሁለተኛ አመቱን የተጠጋ ሰላማዊ ትግል ለጠቅላላ ህዝባዊ አመፅ መሰረት ይሆን?። ይቀጥላል።
May 01, 2013
[email protected]