በሲያትል የኢትዮጵያውያን ፎረም ይመሰረታል

ሰውለሰው (ግንቦት 2003 ዓ.ም) [email protected] 

አቶ መለስ ዜናዊ ”የብልህነቱ” ጥግ አማራንና ኦሮሞን መከፋፈሉ ነው ይባልለታል። ይህ እንዴት ብልህ ሊያሰኝ እንደሚችል አቶ መለስ ዜናዊ ብቻ ያውቃል። እነዚህ ሁለቱ ትላልቅ ብሔረሰቦች በጠላትነት ተፋርጀው እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባይገቡለትም ተባብረው እንዳይቆሙ ለማድረግ በብርቱ ሠርቷል። አቶ መለስ ግድ የለውም፤ ወደ ጎንደር ጎራ ካለ ”ኦሮሞ ሊበላህ እየመጣ ነው” ብሎ በአደባባይ ለመናገር በሰማይ ያለውን እግዜርን አይፈራም። እግር ጥሎት ወደ ወለጋ ብቅ ካለ ደግሞ ”ነፍጠኛ አማራ ሊያጠፋህ እየመጣ ነውና ተጠንቀቅ!” ማለቱን አይረሳውም። እንዲህ በሰው ልጆች መካከል ጥርጣሬንና አለመተማመንን ሲዘራ የሚኖርን ሰው አጃቢዎቹ በምን መለኪያ ”ብልሁ” መሪ እያለ እንደሚያሞካሹት ስናስብ እንገረማለን።