ብር የመግዛት አቅሙ ዝቅ እንዲል ተደረገ

(DW) — ብር አቅም አጥቷል። የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ይባላል። ህብረተሰቡ ኑሮው ከብዷል ይላል። ብር የመግዛት አቅሙ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኑሮውን ሁኔታ ወደባሰ መስመር እንደሚወስደው ባለሙያዎች ይናገራሉ። በኢትዮዽያ በአሁኑ ጊዜ ኑሮ እየናረ እንደመጣ አብዛኛው ሰው ሲናገር ይሰማል። መንግስት የዋጋ ግሽበት መጠን ከዜሮ በታች ደርሷል እያለ በሚገልጽበት በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ ዕቃዎች በተለይም ለምግብነት የሚውሉት ዋጋቸው በአብዝኛው በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ህብረተሰቡ በምሬት ይገልጻል። ከተለያዩ የኢትዮዽያ አከባቢዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ኑሮ ከአቅም በላይ ሆኗል።