ብሔራዊ ባንክ ያሠራቸውን ባለ አንድ ብር ሣንቲሞች ለንግድ ባንኮች አሠራጨ

– ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አውጥቷል

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገልግሎት ላይ የሚገኘውን ባለ አንድ ብር የወረቀት ገንዘብ ለመተካት ያሠራቸውን ባለ አንድ ብር ሣንቲሞች ለመንግሥትና ለግል ንግድ ባንኮች ነሐሴ 19 እና 21 ቀን 2002 ዓ.ም. ማሠራጨቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡