የዘረፋ ውሎ በእንዳማርያም
(ገብረመድህን አርአያ)
ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት። ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል። ብዙም አልደነቀኝም። ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል።