በዓባይ ላይ የመደራደሪያ አቅማችንን እናጠናክር!

የግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት ሐሙስ እኩለ ሌሊት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የሚጐበኙበት ዋነኛው ምክንያት በዓባይ ጉዳይ ለመደራደር እንደሆነም አስቀድመው ገልጸዋል፡፡