አዲሱ የቀጣና ስምሪትና ትርምሱ

ጊዜው ጠዋት ወደ ሥራና ትምህርት መግቢያ ሰዓት ነው፡፡ ሥፍራው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኘው አስኮ መስመር ላይ ነው፡፡ በአንድ ፌርማታ ርቀት ያህል በርካታ ሰዎች የመንገዱን ጠርዝ ይዘው ቆመዋል፡፡