አጀንዳችን አንድ ነው – ሃይማኖታችን እና ቤተ ክርስቲያናችን ብቻ!!!!!!


(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 13/ ሰ2011)፦  ላለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናሳስብ እንደቆየነው ቤተ ክርስቲያናችንን ከፊት ከኋላ፣ ከግራ ከቀኝ እና ከውስጥ ጠፍንገው የያዟት ችግሮች የበለጠ እየተገለጡ፣ ፈተና የሆኑባት ግለሰቦችም የበለጠ እየታወቁ፣ በሕዝቡ ዘንድ ይፈጥሩ የነበሩትም ብዥታና ግርታ የበለጠ እየጠራ በመምጣት ላይ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጪም ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት ቢሆንም ከውስጥ ተቀምጠው፣ እንጀራዋን እየበሉ ተረካዛቸውን የሚያነሱባት ግን ፋታ የሚሰጧት አልሆኑም። እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና የተሰጣቸውን አደራ አራካሾች ሳናሰልስ ተግባራቸውን በመቃወምና ለምእመኑም ለማሳወቅ በመጣር ላይ እንገኛለን። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች የተንጠለጠሉበት ካስማ ደግሞ ሁለት ነው። አንደኛው ሙስና፣ ሁለተኛው ኑፋቄ። ደጀ ሰላምም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሰፈነውን ሙስና ትቃወማለች፣ ሰርገው የገቡትን መናፍቃን እና የሚዘሩትን ኑፋቄ ትጸየፋለች። ምን ማለታችን እንደሆነ እናብራራው።

(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)