የዘረኛው መለስ ዜናዊ ባሌቤት አዘብ መስፍን በእህቷ ልጅ ስም በአገሪቱ ለሚሰሩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ብቸኛ ስምንቶ አቅራቢ በመሆን ብዙ ሚሊዮን ብር ትርፍ እያጋበሰች መሆኑ ተጋለጠ
በግልገል ጊቤ ቁጥር ሁለትና ሶስት እንዲሁም የሚሊየኒየሙ ፕሮጀክት እየተባለ ለሚዘፈንለት ግድብ ግንባታ የስራ ሂደት ዉስጥ የዘረኛውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ባለቤት የአዜብ መስፍን ቀጥተኛ የሙስና እጅ እንዳለበት ላለፉት 6 ወራት ከፍተኛ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ምንጮች ማረጋገጣቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝን ኢሳት ዘገበ። ኢሳት ባሳለፍነዉ ሳምንት እንደዘገበዉ “የሙስና ንግስት” በመባል የምትታወቀዉ የአዘብ መስፍን የሙስና ሰንሰለት በግንባታ ስራዎች፤ በማእድን አቅርቦትና በሌሎችም የተለያዩ ዘርፎች በስፋት የተንሰራፋ ሲሆን ይህንን የሙስና ሰንሰለት የአዘብ ቀኝ እጅ በመሆን በተግባር እየተገበረች የምትገኘዉ አቲኮ ስዩም አምባየ በሚል ስም በምትታወቀዉ የአዜብ መስፍን የእህት ልጅ እንደሆነች ታውቋል። ወ/ሮ አቲኮ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይህ ነዉ የሚባል ኃብት እንዳልነበራት ታሪኳን ያጠኑ የኢሳት ዘጋቢዎች ያረጋገጡ ሲሆን ባለፉት 20 አመታት ግን በእህቷና በእህቷ ባል ልዩ ትዕዛዝ “ወርኪድስ” ቢዝነስ ግሩፕ የሚባል ድርጅት ተከፍቶላት ሆን ተብሎ አያሌ የግንባታ ጨረታዎችን አንድታሸንፍ በመደረጉ የናጠጠች ቱጃር ሆናለች። በርካታ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቧ ከኢህአዴግ አባላትና ከአዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት ያዉቃሉ ሆኖም የአዘብ መስፍን የስጋ ዘመድ መሆኗ እንዳይታወቅ ብርቱ ጥንቃቄ ሲደረግ እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል። የወያኔን በሥልጣን ላይ መፈናጠጥ ተከትሎ በአቋራጭ ከከበሩት የዘመኑ ቱጃሮች አንዷ የሆነችው አቲኮ ስዩምን በቅርብ አውቃታለሁ የሚሉ አንድ አዛዉንት ወ/ሮ አቲኮ በትውልድ ኤርትራዊ በመሆኗ ከአዜብ መስፍን ጋር የንግድ እንጅ የስጋ ዝምድና የላትም ብለዉ መከራከራቸው የተገለጸ ቢሆንም ግለሰቧ በእናቷ የወልቃይት ተወላጅ የአዜብ መስፍን እህት ልጅ መሆኗ ተረጋግጧል። ኤርትራዊነቷ እየተጋነነ የሚወራዉ ከአዘብ መስፍን ጋር ያለቸዉን የስጋ ዝምድና ህብረተሰቡ እንዳያዉቀዉ ሆን ተብሎ የሚነገር የማሳሳቻ ወሬ ነዉ።የአዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆነቺው ወ/ሮ አቲኮ ስዩም በ1992 ዓም የነበራት ንብረት ቢኖር አንድ “ፒካፕ” የኪራይ መኪና ብቻ ሲሆን፣ ዛሬ ግን በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ካፒታል በስሟ እያንቀሳቀሰች መሆኑ ታውቋል።
የአቲኮ አምባዬ ንብረት የሆነው ወርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ የህዳሴዉን ግድብ ፕሮጀክት ኮንትራት አሸነፈ ለተባለው ለሳሊኒ ኩባንያ ዋነኛዉ የሲሚንቶ የአሸዋና የተለያዩ እቃዎችን አቅራቢ በመሆን መመረጡ የታወቀ ሲሆን፣ ይሄው ኩባንያ ለግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ፣ ቁጥር ሁለትና ለሌሎችም ሶስት የሀይል ማመንጫ ግንባታዎች ስሚንቶ ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወስ ነዉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና አዜብ መስፍን በእህቷ ልጅ ስም የምታንቀሳቅሰው ወርኪድ ቢስነስ ግሩፕ የሚባለዉ ኩባንያ በርካታ ንብረት እንዳለው ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ 80 በላይ ዩሮ ትራከር፣ ከ10 በላይ እቃጫኝ ሎቤድ መኪናዎች፣ ከ100 በላይ ገልባጭ መኪናዎችና፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ስካቬተሮች፣ ግሪደሮች፣ ዶዘሮችና የተለያዩ ማሽኖች በስሙ በማንቀሳቀስ ላይ መሆኑኑ ተገልጿል ።አዜብ መስፍን በአቲኮ ኩባንያ ስም የዳሎል ማእድን ማውጫን የምትቆጣጠር ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አዜብ መስፍን አዲስ አበባ ዉስጥ የስፖርት ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ለቁጥር የሚታክቱ ድርጅቶች እንደሏት ታውቋል::