‹‹ማይክሮ ኢንሹራንስን ተደራሽ የሚያደርገው አነስተኛ ገቢ ያለውን ጭምር በማካተቱ ነው››

– አቶ መገርሳ ምሬሳ፣ የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የማይክሮ ኢንሹራንስ ዴስክ ኃላፊ

በአገራችን በአብዛኛው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚታወቁት የመድን አገልግሎቶች ጠቅላላ ኢንሹራንስና የሕይወት ኢንሹራንስ በሚል መጠርያ ነው፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች በአብዛኛው በከተማ አካባቢ የሚሰጡ ናቸው፡፡