ዞምቢዎቹ እየመጡ ነው!
ተመስገንደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ሐምሌ11 ቀንዓ.ም. በታተመችው በ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ወዳጄ መስፍን ነጋሽ ‹‹ዞምቢዎቹ›› በሚል ርዕስ ዛሬም ድረስ ከህሊናዬ ያልጠፋ ድንቅ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር( የዚህ ፅሁፍ ሃሳብም ከዚሁ የተናጠቀነው)፡፡ ይኸ ከሆነ ድፍን ሶስት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል፡፡ ‹‹አዲስ ነገር››ም ወደታሪክነት ከተቀየረች ሁለት ዓመት አልፏታል፡፡ ለምን? …ዞምቢዎቹ ድልስለነሷት፤ እንዴት? ማንም ዞምቢዎቹን ድል አድርጎ ስለማያውቅ፡፡ ዞምቢ ምንድርነው? ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እንዲህ ገልጿቸዋል፡–