ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፭
ጽዮን ግርማ

“… እንዴት አድርጌ ደመወዜን እኮ አልሰጠችኝም፤ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያለች ይኸው እስከ አሁን ታጉላላኛለች። ማታ ማታ በገባች ቁጥር እስከሚበቃት እነግራታለኁ፤ እርሷ መቼ ሰበብ ታጣለች። ቢጨንቀኝ ላገናኘኝ ልጅ ደውዬ ነገርኁት፤ ይብሱኑ እርሱም እኔም ያበደርኋትን አልከፈለችኝም አለኝ። ወይ አሜሪካ! ጉዷን አየኁላት።” መቼም መመረሯ መግለጫ የለውም። …