ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፬
ጽዮን ግርማ
… አባ “አንድ ሰው ጨመርሽልና” አሏት ከትውውቃችን አስቀድሞ አብረው እንዳዩን። “ኧረ ተመላሽ ናት አባ፤ ለሥራ ነው የመጣችው” አለቻቸው። “ትዳር መሥርተሻል?” ጠየቁኝ። “አዎን አባ ቆይቻለኹ” አልኋቸው። ሣቅ አሉና “እኔ ደግሞ ገና ከሩቁ ሳይሽ ልድርሽ እያሰብኹ ነበር፤” አሉኝ ሐሳባቸው ያለመሳካቱ የፈጠረባቸውን ስሜት በፈገግታቸው እየሸፈኑ። …