በኦታዋ ኢሳትን ለመርዳት ከ6500 ዶላር በላይ ተሰበሰበ
ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ተናጋሪ እንግዳ ነበሩ
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2003 ዓ.ም May 2, 2011)፦ የኦታዋ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፡ ከአርብ ኤፕሪል 29 እስከ ቅዳሜ ኤፕሪል 30 ባደረጉት የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የወርሀዊ መዋጮ ቅጽ የሞሉትን ሳይጨምር ከስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር መሰብሰባቸውንና ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋርም የተሳካ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።