ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፫

ጽዮን ግርማ
… ፀጉሯን በፋሽን የተቆረጠች፣ ቀጭን ዝንጥ ያለች ልጅ ቦርሳዋን በአንድ እጇ አስገብታ በአንድ እጇ የስታር ባክስ ቡናዋን እንደያዘች ከአሳንሳሩ ወጣች። የፋሽን ትርኢት በምታሳይ ሞዴል አረማመድ በሽቶዋ አውዳን፣ ማስቲካዋን እያላመጠች በአጠገባችን እልፍ አለች። ከሴቶች ማጌጫ የቀራት ነገር አለ ማለት አይቻልም። እኔ “ልጅቷ” አልኳት እንጂ እሷ እንኳን “ልጁ” ነበረች። በጣም ተገርሜ “ወንድ ነው አይደል?” ስል ወ/ሮ ሐረገወይንን ጠየቅኋት። “አዎ፤ ወንድ ነው፣ ግን ደግሞ ሚስት ነው” አለችኝ። መጸየፏ ከፊቷ ያስታውቃል። …