"መሪዎቻንን የት አሉ?"
በልጅግ ዓሊ
“እኔ ምን አገባኝ የምትለው ሐረግ፣
እሱ ነው ሃገሬን ያረዳት እንደበግ፣
የሚል ግጥም ልጽፍ፣
ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና፣
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና።” ኑረዲን ዒሣ
ጀርመን ፍራንክፈርት በታማኝ በየነ ስብሰባ ታምሳ ከረመች። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ብዙ የፍራንክፈርት አካባባቢ ነዋሪዎች ተገናኝን። አልፎም ተርፎም ችግራችንን ተወያየን። በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ዝግጅት ላዘጋጁት ለወ/ሮ አሳየሽኝና ለአቶ ጥላሁን ምስጋናየን በግሌ አቀርባለሁ።