ኢትዮጵያውያን በጎ አሳቢዎችና ሠሪዎችን ይምረጡ
click here for pdf
የ‹ዳንኤል ዕይታዎችን› ሦስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያውያን በጎ አሳቢዎችና ሠሪዎች ዕውቅና ያገኛሉ፡፡
ለዚህ ምርጫ ‹በጎ አሳቢዎችእና ሠሪዎች› ያልናቸው
- ዕውቀት እንዲሰፋ፣ መልካም ሥነ ምግባር እንዲጎለብት የሚሠሩ
- በተለይም ወጣቱ ትውልድ እንዲያነብ፣ እንዲሠራና እንዲሻሻል የሚጥሩ
- የኢትዮጵያ ስም በዓለም ላይ ከፍ ይል ዘንድ በየመድረኩ የሚተጉ
- በየሚዲያው ሀገራዊ ባህሎች፣ ዕውቀቶችና ታሪኮች በትውልዱ እንዲታወቁ የሚተጉ
- ቅርስ እንዲጠበቅ የሚደክሙ
- በበጎ ፈቃድ ተነሣስተው ለተረሱ ወይም ለተገለሉ የማኅበረሰቡ ክፍሎች በጎ ሥራዎችን የሚሠሩ
- የትምህርት ዕድል ያላገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዕድሉን እንዲያገኙ የሚለፉ
- በሞያቸው ከሚከፈላቸው በላይ የሞያን ሥነ ምግባር ጠብቀው ኅብረተሰቡን የሚያገለግሉ
- እንግዳና አይደፈሬ የሆኑ ነገሮችን በመሞከር አዳዲስ ሃሳቦችን ያመጡና ያስተዋወቁ
- ለሀገራዊ ና ሕዝባዊ ችግሮች ፈጥነው በመድረስና የዐቅማቸውን ሁሉ በመሠዋት የተመሰገኑ
ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ አንዱን፣ ሁለቱን፣ ሦስቱን፣ ወይም ከተቻለ ሁሉንም የሚያሟሉ ኢትዮጵያውያንን ጠቁሙ፡፡
· ስማቸውን፣ ስለ ሥራቸው የምታውቁትንና ከተቻለም አድራሻቸውን፡፡
· የምርጫ ኮሚቴው የእናንተን ጥቆማ በመያዝ መረጃዎችን ካጣራ በኋላ ለእነዚህ ኢትዮጵያውያን በበዓሉ ላይ ዕውቅና በመስጠት ይሸልማል፡፡
· ዓላማው በጎ አሳቢና በጎ ሠሪ ኢትዮጵያውያንን እኛው ራሳችን እንድናበረታታቸው፣ እነርሱን በማበረታታትም ሌሎችን በጎ አሳቢዎችና በጎ ሠሪዎችን ለማፍራት መቻል ነው፡፡
የዕጩ ግለሰቦችን ስም የምትልኩት በሚከተለው ኢሜይል ነው፡፡
ዕጩዎችዎን እስከ መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓም ይላኩ፡፡