ነፃ ፕሬስ የዴሞክራሲ ዋስትና ነው!! ሁሉም ዘብ ይቁም!!

የፊታችን ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ወይም እ.ኤ.አ. ሜይ 3 ቀን 2011 በዓለም ደረጃ የፕሬስ ነፃነት ቀን ይከበራል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በየዓመቱ ሜይ 3 የፕሬስ ነፃነት ቀን ተብሎ እንዲከበር ደንግጓል፡፡ በመላው ዓለምም፣ በአገራችንም ጭምር ይከበራል፡፡