የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርብ ቀን ኢትዮጵያ እመጣለሁ አሉ

–  የግብፅ ልዑካን የዓባይን የቀድሞ ውሎች አጣጣሉ

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻራፍ በመጪዎቹ ሰባት ቀናት ውስጥ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ማስታወቃቸውን አልማስሪ አልዩም የተሰኘው የግብፅ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ ያሉት የግብፅ ልዑካን ቡድን አባላት የቀድሞዎቹን የዓባይ ውሎች እንደማይደግፏቸው አስታወቁ፡፡