አልበሽር እና ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ችሎት

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በዳርፉር ግዛት የጦር ወንጀል እና የዘር ማጥፋት ፈጽመዋል በሚል ሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘዉ አለም ዓቀፍ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ተይዘዉ እንዲሰጡት ከጠየቀ ዓመት አለፈ።

አልባሽርን ግን ለህግ የሚያቀርብ የአፍሪቃ መንግስት እስካሁን አልተገኘም። እንዲያዉም በዚሁ ጉዳይ አፍሪቃዉያኑ ለሁለት እንደተከፈሉ ነው። ባለፈዉ ሳምንት የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ደንብ ፈራሚ ኬንያ አዲስ ህገ-መንግስቷን ስታጸድቅ በተካሄደዉ ስነ-ስርአት የአልበሽር መጋበዝ እያነጋገረ ነው። አፍሪቃዉያን መንግስታት አልበሽርን ይዞ ህግ ፊት ለማቅረብ ምን አገዳቸዉ? አዜብ ታደሰ የቀድሞ ዳኛ አቶ ወልደ ሚካኤል መሸሻን አነጋግራ መልስ ይዛለች። ለማዳምጥ አዚህ ላይ ይጫኑ