የናኒ ሕንጻ ግንባታ በመዘግየቱ ሁዳ ሪል እስቴትን ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ አስወጥቶታል
– ሕንጻው በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል
(በኃያል ዓለማየሁ)
የናኒ ሕንጻ ግንባታ ለረጅም ዓመታት በመዘግየቱ ሕንጻውን በባለቤትነት የሚገነባውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ የሆነውን ሁዳ ሪል እስቴትን ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ሊያስወጣው መቻሉን ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡