የህወሓት ፍጥጫ ቀጥሏል
“አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የህወሓት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ
ኢየሩሳሌም አርኣያ
ሁለት ቦታ የተከፈለው የህወሓት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም “መለስ ህወሓትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው።