በአባይ ግድብ ዙሪያ
ግርማ ካሳ
ቋጠሮ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ አንድ ቪዲዮ አየሁ። በሪያድ ሳውዲ አረቢያ፣ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢትዮጵያውያንን ጠርተው፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ ባነጋገሩበት ወቅት፣ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው። «መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም»፣ «የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 27 ይከበር» የሚሉ መፈክሮች የተጻፉባቸው ነጭ ወረቀቶች ሲውለበለቡ ይታያሉ። ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ፣ ለአባይ ግንባታም በቂ ገንዘብ የተሰበሰበ አይመስልም።