ዶክተሩ የኢትዮጵያ ሆቴል አሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ወድቀው ተረፉ

መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም ቅርንጫፍ መሥርያ ቤት ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ኃይሌ ተስፋዬ አልጋ ከያዙበት የኢትዮጵያ ሆቴል አሳንሰር (ሊፍት) ጉድጓድ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወድቀው ተረፉ፡፡