‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ እንቅስቃሴ አሳታፊነት ይጎድለዋል›› ትምህርት ሚኒስቴር
የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ በሚፈለገው ደረጃ የማያሳትፍ መሆኑን፣ አመራሩም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ሁሉንም ወደንቅናቄ በማስገባት በኩል ሰፊ እጥረት ያለበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡