ወደምዕራብ በሄድን ቁጥር ራዕያችንን እናጣለን

ወደምዕራብ በሄድን ቁጥር ራዕያችንን እናጣለን

ማስታወሻ ከሰሜን አሜሪካ

ችግርና ምሬት እንደ መነሻ – አንደኛ

“በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሀሳብህ አርፎ ከሆነ ብዙ ሥራ ይጠብቅሀል” ይላል ከሁለት ሣምንት በፊት የደረሰኝና በየቀኑ እንደዳዊት የምደግመው የምስኪኑ ጓደኛዬ ደብዳቤ። በጽሁፍና በድርሰት ታሪክ ውስጥ በዚህች አጭር ሕይወቴ እንደተረዳሁት ምሬትንና ችግርን እንደመጻፍ የሚቀል ዓለማቀፋዊ ነገር የለም። ለመጻፍም ለመናገርም የሚቀል ርዕስ – ችግር ነው። ባለጸጋዎቹም፣ ነዳያኑም አገራት የችግራቸው ዝርዝር ተዝቆ አያልቅም። አሁን ካናዳና አውስትራሊያ ችግር ያለባቸው ይመስላሉ? እንደውም እነዚህ ሰዎች ሥልጣኔን ብቻ ሳይሆን ችግርንም ነው እንዴ የሠሩት? እስክትሉ ድረስ ችግር ቤቱን የሠራበት ምድር እዚህ ነው። እንዲሁም ዜናዎቻቸውን ብትሰሙ፣ የሚጻፉትም የሚነገሩትም ምሬትና ችግር ይበዛባቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …