በመደራጀት መብት ጥሰት ላይ የሦስትዮሽ ውይይት እየተካሄደ ነው
– ባለሀብቶች ላይ ጫና የሚያሳድር አሠራር እንዲኖር ይፈለጋል
በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሠራተኞች የመደራጀት መብት ላይ እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለመቅረፍ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ከሠራተኛ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በውይይት ላይ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡