በዴር ሡልጣን ገዳም መንግሥታዊ ትእዛዝ የተሰጣቸው አቡነ ማቲያስ ከባለሥልጣናት እና ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ ነው
- በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ጥሪ ቀርቧል፤
![]() |
| አቡነ ማቲያስ |
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 16/2011)፦ በዴር ሡልጣን ገዳም “የኮፕት መነኩሴ በቀዳም ስዑር ሻማ አብርቶ ይዞ ይለፍ” የሚል መንግሥታዊ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ ነው:: በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ እና ማኅበር አባላት ግብጻዊው የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መነኩሴ በበዓለ ትንሣኤ ዋዜማ (ቀዳም ሥዑር) ከጎልጎታ – የጌታ መቃብር ሻማ አብርቶ ይዞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ይዞታ በሆነው በዴር ሡልጣን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ገብቶ በመድኃኔ ዓለም እና አርባዕቱ እንስሳ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለውስጥ አልፎ ወደ ኮፕቲክ ገዳም እንዲገባ ፈቃድ እንዲሰጠው ካዘዙት የእስራኤል መንግሥት ባለሥልጣናት እና ትእዛዙን በግድ ለማስፈጸም ከሚዝቱት የብሉይ ከተማ ኢየሩሳሌም ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
