ፍቅርና አንድነት ያለው ህዝብ ጠላቱን ያሸንፋል
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ባለፈው ሂትለርና የወያኔን መሪዎች ባነጻጸርኩበት ጽሁፍ ላይ መለስ ስብሀት በአማራው ህዝብ ላይ በሰፊው ሊያንቀሳቅሱ የሞከሩት እልቂት አንዴት በሚፈልጉት ልክ እንዳልገፋላቸው ሗላ ላይ እናወጋለን ብየ ነበር። በአለማችን ያሉ ጤናማ መንግስታት በዜጎቻቸው መካከል የመብት ልዩነትና የዘር የቀለም መለያየት፤ ግጭት እንዳይኖር ያለመታከት ይሰራሉ። ይተጋሉ። በኢትዮጵያ ያለው የዲያቢሎሶች መንግስት፤ ሰው በዘሩ ተለይቶ እንዲታወቅ፤ እንዳይስማማም እንዲበላላም ለማድረግ በትጋት ሲሰራ ሀያ ሁለት አመታትን አስቆጠረ።