የኢትዮጵያ እግር ኳስና የደረደሩት ችግሮቹ (ሰሎሞን ተሰማ ጂ.)
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የኢትዮጵያን አግር ኳስ በዋናነት የሚፈታተኑት ችግሮች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ዋና ዋናዎቹን የስፖርቱን እንቅፋቶች ለማውሳትም ያህል እንሞክራለን። ችግሮቹን በሦስት ረድፍ ደርድሮ ማየቱ ይበጃል። የመጀመሪያውና ዋናው የፖለቲካውና የፖለቲከኞቹ ብልጣብልጥነት ስሜት ነው። ይህም ብልጣ ብልጥነት በአንደኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ተንፀባርቆ ነበር። ሁለተኛው ችግር ደግሞ፣ የፌዴሬሽኑና የተጫዋቾቹ የብሔራዊ ስሜት የማጣት ችግር ነው። በሦስተኛ ደረጃም ተጠቃሽ የሚሆነው የስፖርት ጋዜጠኞቹና የሕዝቡ ድጋፉን በተገቢው ኹኔታ አለመስጠቱ ናቸው። እነዚህ ችግሮች እርስ በርሳቸው የተያያዙ በመሆናቸው፣ ስለአንዱ ስናነሣ ስለሌላኛውም እያወሳን እንደሆነ ትገነዘባለችሁ። በመጽሔታችን ገጽና ዐምዶች ሙሉ ለሙሉ ተሸፍኖ የማያልቅም ስለሆነ (ራሱን ችሎ ጥናትና ምርምር ያስፈልገዋል)፣ ቀሪዎቹን ነጥቦች እናንተ አንባቢያኑ በጎደለ እንድትሞሉልን በትህትና እንጠይለን።