ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በአረብ ሀገር… (ግሩም ተ/ሀይማኖት)

በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል

ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ

ዕለት ከዕለት በየመን ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ ላይ የሚሰራው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትና ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ሀገሬ የገቡት በየመን በኩል ነው እና ወደ ሀገራቸው ሳይሆን ወደ የመን ነው የምመልሰው ብሏል። ማለት ብቻም አይደለ አፍሶ እያመጣ የመን መሬት ቀይ ባህር ዳርቻ እየጣላቸው ነው። ከሳዑዲ ተመላሾቹን ገንዘብ ይዘዋል። ባይዙ እንኳን እዛ ካለ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ ያስልካሉ ብለው እያፈኑ ማሰቃየቱን በግሩፕ የተደራጁት የመናዊያን ገፍተውበታል። ከሳዑዲ ተመላሾቹ ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ከመምታት ጀምሮ በመኪና ሁሉ እየገጩ በመግደል መጫዎቻ አድርገዋቸዋል። ይህን ስራ በትብብር አብረዋቸው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ያነጋገርኳቸው ልጆች ነግረውኛል።