የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና አባ ዝምታዎች ትንሣኤ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በአቦሸማኔዎች ምድር የጉማሬዎች (አባ ዝምታዎች) ዓለም

በአዲስ ዓት መግቢያ ጦማሬ ላይ 2013ን “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ዓመት”(የወጣቶቹ) ብዬው ነበር። በዚህ ዓመትም የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ባሉበት ለመድረስ፤ ለማሳሰብም ቃል ገብቼ ነበር። የኢትዮጵያም የምሁራን አምባ ይህንኑ ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኜ ነበር (በተለይም በከፍተኛው ጣርያ ላይ ያለነውን ምሁራን)። በተመሳሳይ ወጣቱን እንዲደርሱት አሳስቤም ነበር። ከዚህ ባለፈም ተማጽኖዬ ከሰፊው የጉማሬ ትውልድ ጋር (መንገዱ የጠፋው ትውልድ) እራሱን በማግኘት መስመሩን አስተካክሎ ጉዞውን እንዲያሳምርና ወጣቱን እንዲረዳ ምኞቴን አስታውቄ ነበር።