ኳስና ፖለቲካ

የኢትዮጵያዊነት ልዩ ውበትና አንድነት እስከ ፖለቲካዊ፣ ኃይማኖታዊ፣ የመብት ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች የተንጸባረቁበት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

Sports had the power “to change the world … to inspire … to unite people.” – Nelson Mandela

ፍቅር ለይኩን

የ998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት … ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው። በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋኗ እስከ አስር ሺህ ዘመን በሚመዘዝ ግዙፍ ታሪኳ፣ ታላቅ የሆነ ብሔራዊ ኩራትና ስሜት ያላት ጥንታዊቷ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ ከአሜሪካ አቻዋ ጋር በተፋጠጡበት መድረክ፣ የትናንትነዋ ኃያል ኢራንና የዘመናችን ልዕለ ኃያል አገር አሜሪካን ያገናኘ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ነበር ያለፈው።