የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን መንግሥት ገለጸ

– ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች

በዘካሪያስ ስንታየሁ

አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡