የኤርትራ መንግስት አደጋ ላይ ወድቋል

Presidant Isaias Afewerki ፕሬዝዳንት ኢሣያስ አፈወርቂየፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ ሴት ልጅም ታግዳለች

በአገዛዙ የተማረሩ ወታደሮች የቴሌቭዥን ጣቢያውን ተቆጣጥረውት ነበር

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም. January 22, 2013)፦ ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ የኤርትራ መንግስት ወታደሮች መንግስታቸውን ተቃውመው በትናንትናው ዕለት ሰኞ ጀንዋሪ 21/2013 ዓ.ም. የማስታወቂያ ሚንስቴሩን መ/ቤት ከበው በቁጥጥር ስር አውለዋል። የፖለቲካ ተሀድሶ እንዲደረግና የህሊና እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ሀሳብ እንዳላቸውም አስታውቀዋል።