አስገድዶ መድፈርን ያጋለጡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ ጉዳይ

አንዲት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በተማሪዎች አገልግሎት ዲን ተደፈረች ስለተባለበት ወንጀል ለዶይቸ ቬለ መረጃ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ አቶ ደማስ ካሳ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ትዕዛዝ ከስራቸው እና ከደሞዝ ታገዱ።