ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?

አቤ ቶኪቻው

የቀድሞው አለቃዬ እና የአሁን ወዳጄ ዳዊት ከበደ ሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ ሰንብቷል። ለምን አወዛገበ? ምን አወዛገበ? እንዴት አወዛገበ? ማንን አወዛገበ…? ወዘተ የሚሉትን ሁሉንም ዘርዝሬ መዝለቄን እንጃ ግን እስቲ ትንሽ ነካ ነካ ላድረግማ፤ ባለፈው ጊዜ ዳዊት ከበደ ስለ ኢትዮ ሚዲያው አበርሃ የፃፈውን ወቀሳ በአውራምባ ታይምስ ድረ ገፅ ላይ አንብቤ ነበር። በኢትዮ ሚዲያ ላይ ስለ ዳዊት ከበደ የወጣውን ፅሁፍ አላየሁትም። የዳዊትን ምላሽ ግን አልወደድኩትም። ይህንን ለዳዊትም ነግሬዋለሁ። ሳስበው ዳዊት ያንን ፅሁፍ ሲፅፍ ክፉኛ ተበሳጭቶ እንደሆነ እገምታለሁ። ምን መገመት ብቻ በደንብ አውቂያለሁ እንጂ…