ይድረስ የመን ላላችሁት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች
ሀበሻ በየመን ክፍል 10
ሀገር መግባት ለሚፈልጉ መርዳት ከቻላችሁ…
በግሩም ተ/ሀይማኖት
መጠ ሰው ወገን ወገኑን ሲባላ ወገን ወገኑን ሲረዳ ያያል፡፡ በሁለቱም መንገድ ተሰለፉም አሉ፡፡ አንዱን ይበላሉ አንዱን ይረዳሉ፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን ወገን ወገኑን ማረዱ፣ ለማጥፋት መቸኮሉ የሚያሳዝን ነው፡፡ በተለይ ለኢትዮጵያዊያን ይሰራል የተባለው ስሙን ኤምባሲ ያደረገው የሆድ አደር ጥርቅም ግሩፕ ወገኑን ሲገፋ እና ሲደፋ ማየት አስጠሊታ ነገር ነው፡፡ ይህን ያልኩበት ምክንያት አለኝ፡፡ ይድረስ ስል ‹‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት..›› የሚሉትን አባባል ረስቼው አይደለም፡፡ ወይም ህሊናችሁን በሆዳችሁ እንደ ቀየራችሁት ዘንግቼም አይደለም፡፡