የ “ሪፖርተር” አዘጋጅ አማረ አረጋዊ ማላገጥህን አቁም!

እየሩሳሌም አርአያ

አማረ አረጋዊን የማውቀው ጋዜጣውን ሲጀምር ነው፤ አብሬው ለሶስት አመት ሰርቻለሁ። …አማረ የግል ጥቅሙ እስካልተነካ ድረስ በአገርና ሕዝብ ላይ የፈለገ ነገር ቢፈፀም ደንታ አይሰጠውም። “ፍትሕ” እና “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጦች ከህትመት ውጭ ሲደረጉ « የፕሬስ ነፃነት ይከበር» ብሎ አንድ መስመር በርዕሰ አንቀፅ አልፃፈም፤ እንዲያውም የ “ፍኖተ ነፃነት” አዘጋጆች ስለጉዳዩ አማረን ሲያናግሩት በረከትና ሽመልስ ከሚሰጡት መልስ ጋር የሚመሳሰል ምላሽ በማመናጨቅ ጭምር ነበር የሰጠው።